በሀገሪቱ በኤችአይቪ\ኤድስ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2005/ዋኢማ/ -በሀገር አቀፍ ደረጃ በኤችአይቪ ኤድስ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን የፌዴራል ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽህፈት ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መስቀሌ ሌራ ዛሬ በጋራ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለፁት፤ በቫይረሱ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 0 ነጥብ 9 በመቶ ቀንሷል፡፡
ለተገኘው ውጤትም መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ህብረተሰቡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ጠቁመው፤ በተለይም መንግስት ግልፅ የሆነ እስትራቴጂክ እቅድ በመቅረፅ በጠንካራ አመራር ተግባራዊ በማድረጉ ነው ብለዋል፡፡
የቫይረሱን ስርጭት ይበልጥ ለመከላልና ለመቆጣጠርም የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፤ በተለያዩ ዘርፎች ለማሳካት የታቀደውን እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከግብ ለማድረስ ወጣቱ ትውልድን ከቫይረሱ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አቶ መስቀሌ ተናረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጤናና ስነ-ምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ይበልጣል አሰፋ በበኩላቸው፤ በአጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱም ስለ ኤችአይቪ ኤድስ አጠቃላይ ጥናት እንደሚያደርግ ተናግረው፤ በዚህ መሰረትም በአሁኑ ወቅት ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ውስጥ 1 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት አዋቂዎች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የቫይረሱ ስርጭት በወንዶች 1 በመቶ ሲሆን በሴቶች ደግሞ 1 ነጥብ 9 በመቶ መሆኑን ጠቁመው፤ የቫይረሱ ስርጭት በከተማና በገጠር ያለው እንደሚለያይ ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም በከተማ ያለው የቫይረሱ ስርጭት 4 ነጥብ 2 በመቶ ሲሆን፤ በገጠር ደግሞ 0 ነጥብ 6 መሆኑን ዶክተር ይበልጣል ገልፀዋል፡፡
እንዲሁም የቫይረሱ ስርጭት ወንዶች ጋር 1 በመቶ ሲሆን፤ የሴቶች ጋር ደግሞ 1 ነጥብ 9 መሆኑን ገልፀው፤ ሴቶችን በመከላሉ በኩል የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳበት አሳስበዋል፡፡
በክልሎች ያለው የቫይረስ ስርጭት ሲታይም ልዩነት እንዳው ገልፀው፤ የደቡብ ክልል የቫይረሱ ስርጭት በተወሰነ መልኩ ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነፃፀር በተወሰነ መልኩ የቀነሰ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
በኤችአይቪ ኤድስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም እየቀነሰ መምጣቱን ኢንስቲትዩቱ ባደረገው ጥናት ማረጋገጥ መቻሉን ዶክተር ይበልጣል በመግለጫው ላይ ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ታደሰ አጥላባቸው በበኩላቸው በከተማዋ የኤችአይ ቪ ኤድስን በመከላከልና መቆጣጠረት ረገድ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው፤ በዚህም የበሽታው ስርጭትን ቀደም ሲል ከነበረበት 9 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 5 ነጥብ 2 በመቶ ዝቅ ማድረስ ተችሏል ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በከተማዋ 53ሺ 500 የሚሆኑ ወገኖች ነፃ የኤችአይቪ ኤድስ ህክምና እያገኙ ያሉበት ሁኔታ መኖሩን ገልፀው፤ ህክምናውን የሚሰጡ ተቋማት ቁጥርንም 47 የነበረውን ወደ 83 ማሳደግ ተችሏል ብለዋል፡፡
ሌላው ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የሚያስችሉ የነፃ ህክምና የሚሰጡ ተቋማት ቁጥርን የማሳደግ ስራ መሰራቱን ገልፀው፤ ቀደም ሲል 44 የነበረውን በአሁኑ ወቅት ወደ 120 በማሳደግ አገልግሎቱን እየሰጡ ይገኛሉ በማለት ተናረዋል፡፡
በፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር ፍሬህይወት ንጋቱ በበኩላቸው፤ በሀገሪቱ የኤችአይቪ/ኤድስን በመከላልና በመቆጣጠር በኩል የተሻለ ውጤት ለማምጣትም አዳዲስ እቅዶችን በማዘጋጀት ወደ ተግባር እየተገባ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመግለጫው ላይ የኢትዮጵያ የምግብና የመድሀኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የመድሃት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ፣ የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክ ፖዘቲብ ፒፕል እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የሚመለከታቸው አካላት መገኘታቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር