በብራዚል የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ኢትዮጵያ የቡና ገበያውን ለመምራት መዘጋጀቷ እየተነገረ ነው፤ ለመሆኑ የቡና ኣብቃይ ኣርሶ ኣደሮች ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ምን ታስቧል?

በዓለም ላይ ከፍተኛውን ቡና በምታቀርበው ብራዚል የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ኢትዮጵያ የቡና ገበያውን ለመምራት መዘጋጀቷ እየተነገረ ነው። ለዚሁም የኣገሪቱ መንግስት እና ቡና ላኪዎች ከኣጋጣሚው ተጠቃሚ ለመሆኑ በመስራት ላይ መሆናቸው ታውቋል። ለመሆኑ የቡና ኣብቃይ ኣርሶ ኣደሮች ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ምን ታስቧል? 

የኣገሪቷን የቡና ኣቅርቦት ለማሳደግ በመሰራት ላይ መሆኑን በተመለከተ የቀረበ ዘጋባ፦
በዓለም ላይ ከፍተኛውን ቡና በምታቀርበው ብራዚል የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ኢትዮጵያ የቡና ገበያውን ለመምራት እንደተዘጋጀች የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ገለጸ።
የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ሁሴን አግራው እንደሚሉት በጎርጎሮሳውያኑ 2014/15 መጨረሻ ከ235 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለውጭ ገበያ በማቅርብ 8 መቶ 62 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት እየተሰራ ነው።
በብራዚል የተፈጠረውን የቡና ምርት መቀነስ ምክንያት በማድርግ ኢትዮጵያ በሰፊው ለዓለም ገበያ ቡናን ለማቅረብ እንደምትሰራ ገልጸዋል።
ከለፈው ሐምሌ  ጀምሮ ባሉት አራት ወራት ኢትዮጵያ 54 ሺህ ቶን ቡናን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሆናለች።
ከዚህም 2 መቶ 32 ሚሊየን ዶላር  ገቢ ማግኘት ችላለች፡፡ ይህ አሃዝ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ59 ሚሊየን ዶላር በላይ ብልጫ አለው።
ምንጭ፦ ኢብኮ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር