ደኢህዴን ሲአንን ከሰሰ

በደቡብ ክልል በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ለመወዳደር የጋራ ምክር ቤት የመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ አካሄዱ፡፡
ምክር ቤቱ ሲአን መድረክ አወጣ በተባለው መግለጫ ላይ መልስ እንዲሰጥ በወሰነው መሰረት መልስ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
መጋቢት አስር ቀን 2007 በተካሄደው የመጀመሪያው ዙር አስቸኳይ ስብሰባ ሲአን መድረክ የጋራ ምክር ቤቱን መተዳደሪያ ደንብና የምርጫ ህጉን በመጣስ ህዝብን በህዝብ ላይ የሚያነሳሳና ጭብጥ የሌለው መግለጫ አውጥቷል በሚል በደኢህዴን ኢህአዴግ ክስ አቅርቦ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
Image result for EPRDFበዛሬው ስብሰባ ደኢህዴን ኢህአዴግ የሲዳማ ብሄር ተወላጅ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለግጭት ሊያነሳሳ የሚችል የሚስጥር ደብዳቤ አውጥቷል በሚል ተጨማሪ ክስ በደኢህዴን የከተማ ህዝብ ፖለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በአቶ አብርሐም ማርሻሎ ለጋራ ምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡
በሰብሰባው የሲአን መድርክ ዋና ጸሀፊ አቶ ለገሰ ላንቃሞ በጽሁፍ በሰጡት መልስ እንዳሉት ተከሳችኋል የተባልንበት ክስ ጭብጥ በከሳሽ ደብዳቤና ፊርማ ያልደረሰን በመሆኑ በጋራ መድረኩ የወጣው መግለጫ የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ጥሰት መፈጸሙን ያረጋገጠበትን ለፓርቲያችን በግልጽ ባለማሳወቁ የጋራ መድረኩ ክሱን ተመልክቶ የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ጥሰት መኖሩን አረጋግጦ ክሱ በጽሁፍ እንዲደርሰን በመጠየቅ ምንም ክርክር ባልተሰማበት ጉዳይ በተሰጠብን የጥፋተኝነት ውሳኔ ላይ ምላሽ መስጠት አንችልም ብለዋል፡፡
ከጋራ መድረኩ አባል ፓርቲዎች መካከል የኢዴፓ የደቡብ ክልል ምክትል ሰብሳቢ አቶ ወልዴ ካሳ እንዳሉት የሲአን መድረክ መግለጫ ከምርጫ ጋር የማይገናኝና የመንግስት ጉዳይ በመሆኑ መሰረተ ቢስና በአቋራጭ ምርጫ ትርፍ ለማግኘት ብሎ ያደረገው ነው፡፡
በጋራ ምክር ቤቱ ሰፊ ውይይት የተደረገ ቢሆንም ውሳኔ ለመስጠት የጋራ አቋም ላይ መድረስ ባለመቻሉ ደኢህዴን ያለውን ማስረጃ በማሰባሰብ ክሱን ለምርጫ ቦርድ እንደሚያቀርብ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ሁሴን ኑረዲን አስታውቀዋል፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ በቀጣይ ሳምንት የሚያደርገውን መደበኛ ስብሰባ የኢራፓ ተወካይ በሰብሳቢነት እንዲመሩ በመምረጥ ተጠናቋል፡፡
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/politics/item/3056-2015-03-25-00-19-19#sthash.Pm8lhVvm.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር