Earthquake Reported near Hawassa City - Jan 24, 2016

A Very Scary Earthquake reported Hawassa City, Ethiopia at 10:02PM on Jan 24, 2016. No major injuries or death was reported.
http://www.diretube.com/uploads/articles/8b77a0bc.jpg
አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) በሬክተር ስኬል መለኪያ 4 ነጥብ 3 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በሀዋሳ እና አከባቢው ትናንት ምሽት ተከስቷል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በዋናነት ከከተማዋ ደቡብ ምእራብ አቅጣጫ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ ሲሆን፥ የመንቀጥቀጡ ንዝረት ሀዋሳን ጨምሮ በአከባቢው ባሉ ከተሞች ተሰምቷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ ባለሙያው ዶክተር አታላይ ዓየለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የመሬት መንቀጥቀጡ ሁለት ጊዜ ነው የተከሰተው።
የመንቀጥቀጡ ንዝረት ስፋት እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች እየተጠኑ መሆናቸውን ዶክተር አታላይ ተናግረዋል።
ዛሬ ረፋድ ላይ በአከባቢው ንዝረት እንደነበር የተረዳን ሲሆን፥ ዶክተር አታላይ ትናንት የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በተደጋጋሚ ንዝረቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ነው የጠቆሙት።
ይህም ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማያደርስ የአከባቢው ነዋሪ ተረድቶ ምንም እንዳይሸበር አሳስበዋል።
በከተማዋ የመኖሪያ መንደር በሆኑ የኮንዲሚኒየም ቤቶች አከባቢ ከቤት እቃ የማውጣት ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፥ ህብረተሰቡ ዋናው የመሬት መንቀጥቀጥ ከተከሰተ በኋላ የሚኖር ንዝረት እንዳለ ተገንዝቦ ሊረጋጋ እንደሚገባም ነው ያመለከቱት።
ዛሬ ላይ የነበረው ንዝረት እጅግ ዝቅተኛ በመሆኑን የመለኪያ መሳሪያው ራሱ እንዳልመዘገበው ዶክተር አታላው ገልፀዋል።
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴድሮስ ገቢባ እንደገለፁልን፥ በትናንቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች ዘንድ በተፈጠረው ድንጋጤ ከህንፃ ለመውረድ ሲሞክሩ 100 የሚሆኑ ተማሪዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ከእነዚህ ተማሪዎች መካከልም 90 የሚሆኑት የመጀመሪያ እርዳታ አግኝተው ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለሳቸውንም ነው ከንቲባው ያመለከቱት።
በከተማዋ አንዳንድ ሀንፃዎች በመንቀጥቀጡ መሰንጠቅ እንደተስተዋለባቸውም ነው የገለፁት።
የሀዋሳ ከተማ እና አከባቢዋ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው ከዚህ በፊት መሰል የመሬት መንቀጥቀጥ በአከባቢው ተከስቶ ያውቃል።
- See more at: http://www.fanabc.com/index.php/news/item/13302-%E1%89%B5%E1%8A%93%E1%8A%95%E1%89%B5-%E1%88%9D%E1%88%BD%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%88%80%E1%8B%8B%E1%88%B3%E1%8A%93-%E1%8A%A0%E1%8A%A8%E1%89%A3%E1%89%A2%E1%8B%8B-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%88%AC%E1%89%B5-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%89%80%E1%8C%A5%E1%89%80%E1%8C%A5-%E1%89%B0%E1%8A%A8%E1%88%B5%E1%89%B7%E1%88%8D.html#sthash.u9amhN89.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር