አቢሲኒካ መዝገበ ቃላት ABYSSINICA DICTIONARY ሲዳማን ስበይነው Get link Facebook Twitter Pinterest Email Other Apps November 14, 2016 ምንጭ፦http://dictionary.abyssinica.com/%E1%88%B2%E1%8B%B3%E1%88%9B Get link Facebook Twitter Pinterest Email Other Apps Comments
ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ November 01, 2014 የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡ የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡ ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ Read more
የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት September 01, 2019 የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል Read more
በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር October 01, 2022 በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳይ ላይ ከገዢው ፓርቲ አመራር ጋር ምክክር አካሄዱ። የምክክር ተሳታፊዎች በበኩላቸው የውውይት መድረኩ በመሀል አገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የሚያጋጥማቸውን የደህንነት ሥጋት ለመቅረፍ እንደሚያስችል ተናግረዋል:: በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ዛሬ ከሲዳማ ክልል ገዢው ፖርቲ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ የሲዳማ ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብረሃም ማርሻሎ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተካሄደ በሚኘው ጦርነት መነሻና አሁን ያለበትን ሁኔታ ለተሳታፊዎቹ ገለጻ አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አገር ሊያፈርስ ተነስቷል ያለውን የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ህወሃትን እየታገለ እንደሚገኝ የጠቀሱት አቶ አብረሀም ለዚህም የትግራይ ሕዝብ በጋራ አብሮ ሊቆም ይገባል ብለዋል፡፡ የውይይት መድረኩ ያሥፈለገው በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የጋራ መግባባት ለመያዝ መሆኑን የገለፁት አቶ አብረሀም ተሳታፊዎቹ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ጋብዘዋል፡: አብዛኞቹ የውይይቱ ተሳታፊዎች ጦርነቱን እንደሚያወግዙ የገለፁ ሲሆን በትግራይ የሚገኘው ሕዝብ ግን የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራሮችን ለመቃወም በሚችልበት ሁኔታ ውስጥ አይደለም ያለው ብለዋል፡፡ ሳጅን ገብረኪሮስ ሞገስ እባላለሁ ያሉ አንድ የውይይቱ ተሳታፊ አዛውንት ከትግራይ ክልል አምልጦ ሰቆጣ አካባቢ የገባ አንድ የእህቴን ልጅ በስልክ አውርቼው ነበር ካሉ በኋላ ‹‹ አሁን ላይ ትግራይ ውስጥ አንዱ በሌላው ስለሚሰለል ስለህውሃት ምንም አይነት ነቀፌታ ያለው አስተያየት መስጠት ሕይወት ሊያሳጣ እንደሚችል ገልጾልኛል ›› ብለዋል፡፡ እኔም ብሆን ህወሃት እየካሄደ የሚገኘውን ጦርነት እዚህ መቃወምና ማውገዝ እችላለሁ እዛ Read more
Comments
Post a Comment