የቡና ጣዕም ያለው ሲዳማ ቢራ ሰሞኑን በኣገረ ስፔን መመረት ጀምሯል። ለመሆኑ የህዝብ መጠረያ ስም ለምርት መጠሪያነት መጠቀም ይቻላል ወይ?

sidama Althaia artesana
ፎቶ ከAlthaia
የቡና ጣዕም ያለው ሲዳማ ቢራ ሰሞኑን በኣገረ ስፔን መመረት ጀምሯል። ሲዳማ ቢራን ምርት የጀመሩት D·Origen Coffee Roasters እና Althaia Artesana ተባሉት ሁለት የስፔን ኣገር ኩባኒያዎች ናቸው። ኩባኒያዎቹ ቡናን ቆልቶ እና ፈጭቶ በማዘጋጀት የሚያከፋፍሉ፤ ብሎም የተለያዩ ጣዕሞች ያላቸው የቢራ ኣይነቶችን በማምረት የሚታወቁ ናቸው።

የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ከኩባኒያዎቹ ድረገጽ ላይ ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደምያመለክቱት፤ ሲዳማ ቢራ SIDAMA – BROWN COFFEE PORTER ተብሎ የምጠራ እና የሲዳማ ቡና ከሌሎች ለቢራ መስሪያነት ከሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮች ጋር ተደባልቆ የሚዘጋጅ ነው ። ቢራው በቅርቡ ተቆልቶ የተፈጭ የሲዳማ ቡና ጣዕም የያዘ እና 58% የኣልኮል ይዘት ያለው ነው።

እንደ ኩባኒያው ከሆነ፤ ቢራው በሲዳማ ስም የሚጠራ ቢሆንም ለቢራው መስሪያነት ጥቅም ላይ የሚውለው ቡና ምንጩ ግን ሲዳማ ሳይሆን የኦሮሚያው ጉጂ ዞን ነው።

ለመሆኑ ኣንድ ከሲዳማ ያልሆነ ድርጅት ወይም ኩባኒያ ምርቶቹን በሲዳማ ህዝብ ስም መጥራት ይችላልንይህንን በተመለከተ የሕግ ባለሙያዎች ምን ይላሉ

ለተጨማሪ መረጃ ከታች ይጫኑ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር