የጋራ ምክር ቤቱ በኣገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየትና ችግሮችን ለመፍታት እድል ፈጥሯል-ፓርቲዎች
የጋራ ምክር ቤቱ በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከገዥው ፓርቲ ጋር በሰከነ መንፈስ ለመወያየትና ችግሮችን ለመፍታት እድል ፈጥሯል-ፓርቲዎች አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከገዥው ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራትና በመካከላቸው የሚከሰቱ ቅሬታዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እድል መፍጠሩን አንዳንድ አባል ፓርቲዎች ገለፁ። በጋራ ምክር ቤቱ ያልተካተቱ ፓርቲዎችም በአገሪቱ የተጀመረው የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዲጠናከር የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ካነጋገራቸው የጋራ ምክር ቤቱ አባል ፓርቲዎች መካከል የአዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) ፕሬዝዳንት አቶ አስፋው ጌታቸው ከገዥው ፓርቲ ጋር የሚደረገው ውይይት በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በፓርቲዎች መካከል መግባባትን ከመፍጠር ባለፈ የመጪውን ትውልድ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ለማዳበር የጎላ ሚና አለው ብለዋል። ፓርቲዎች በአንድ አገራዊ ጉዳይ ላይ የሰከነ ውይይት ማድረጋቸው በመካከላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በቀላሉ እልባት ከመስጠቱም ባሻገር ለመደብለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዓቱ መጠናከር የማይተካ ድርሻ አለው። በምክር ቤቱ ውስጥም የሁሉም አባል ፖለቲካ ፓርቲዎች አገራዊና ድርጅታዊ አጀንዳዎች እንደሚስተናገዱ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ጠንካራ ክርክሮችን በማድረግ ለህዝብ የሚቀርቡ አማራጭ ሃሳቦች ጎልተው እንዲወጡ ይደረጋል ብለዋል። አቶ አስፋው እንዳሉት እስከታችኛው የስልጣን እርከን ድረስ የምክር ቤቱ አባላት ለሚያነሷቸው ችግሮች ከሁሉም ፓርቲዎች የተውጣጡ አጣሪ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ዘላቂ እልባት እንዲኖር እድል መስጠቱንም ጠቅሰዋል። በጋራ ምክር ቤቱ የተቋቋመው ኮሚቴ በተከሰቱ ችግሮች ዙሪያ የሚያቀርበው ሪፖርት በመነሳት ገዥ