Posts

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲስተካከል እንግሊዝ ጥያቄ አቀረበች

Image
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ እየተፈጠሩ ያሉ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግሮች እንዲስተካከሉ እንግሊዝ ጠየቀች፡፡   የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሒሩት ዘመነ ከእንግሊዝ አምባሳደር ሱዛና ሞርሄድና ከኤምባሲው የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ እየተከሰተ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግር እንዳለ፣ ኢትዮጵያም ይህን ችግር እንድታስተካክል እንግሊዝ ምክረ ሐሳብ ማቅረቧ ታውቋል፡፡ ይህ ምክረ ሐሳብ የቀረበው ኢትዮጵያና እንግሊዝ ለአራተኛ ጊዜ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ያተኮረ የጋራ ውይይት፣ ሰኞ ኅዳር 4 ቀን 2010 ዓ.ም. በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡ በውይይቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሒሩት ዘመነ፣ በኢትዮጵያ የስደተኛና ከስደት ተመላሽ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተወካዮች፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ሱዛና ሞርሄድና የኤምባሲው የሥራ ኃላፊዎች፣ የብሪታኒያ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (ዲኤፍአይዲ) ዳይሬክተሮችና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተገኝተው ነበር፡፡ የውይይቱ አጀንዳዎችም የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ ስደት፣ የመንግሥት ተጠያቂነትና ግልጽነት ነበሩ፡፡ የሁለቱ አገሮች የጋራ ውይይት የተካሄደው በዝግ ቢሆንም፣ የሪፖርተር ምንጮች እንደጠቆሙት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ያሉ ችግሮችን የእንግሊዝ መንግሥት ተወካዮች በዝርዝር አውስተዋል፡፡ አንድ የእንግሊዝ ዲፕሎማት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ስደተኞችን በማስተናገድ ግንባር ቀደም አገር ብትሆንም በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ችግሮች አሉባት፡፡ ‹‹ይህንን ያህል የስደተኛ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

Image
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ከቦንድ ግዥ በተጨማሪ በምርምር ስራ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡ የህዳሴ ግድቡን ዋንጫ አቀባበል ምክንያት በማድረግ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራንና ሰራተኞች ለግድቡ ግንባታ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አቶ አያኖ በራሶ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ድጋፉን አጠናክሮ ለመቀጠል ቃል ገብቷል፡፡ የህዳሴ ግድቡ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ በቦንድ ግዥ፣ በዕውቀትና በክልሉ በግድቡ ዙሪያ በሚደረጉ የውይይት መድረኮች የተቋሙ ምሁራን ሙያዊ ማብራሪያ በመስጠት ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በምርምር ረገድም ራሱን የቻለ የውሀ ዘርፍ እንዳለው ጠቁመው በቀጣይም የአባይ ውሀ ሀገሪቱ የበለጠ መጠቀም የምትችልበትን ሁኔታን በጥናት በመለየት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አቶ አያኖ ገልጸዋል፡፡ የህዳሴ ግድቡ ዋንጫ ሀዋሳ መግባቱን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራንና ሰራተኞች በስጦታና በቦንድ ግዥ ከ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውንም አመልክተዋል፡፡ በግላቸው ለሶስተኛ ጊዜ በወር ደመወዛቸው የቦንድ ግዥ መፈጸማቸውንም ጠቁመዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የኬሚስትሪ የትምህርት መስክ የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ዮርዳኖስ ገብረስላሴ በበኩሏ የአባይ ወንዝ ለሀገሩ ጥቅም እንዲሰጥ የግድቡ መገንባት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሳ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ወደ ዩኒቨርሲቲው መምጣቱ እንዳስደሰታት ተናግራለች፡፡ የኮምፒውተር ሳይንስ የአራተኛ ዓመት ተማሪው  ታደሰ አይጠገብ በሰጠው አስተ